Latest News

በግብጽ የኮፕቲክ ክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች ላይ በደረሰው የሽብር አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ገለፁ፡፡

In this Edition

በግብጽ ታንታ እና አሌክስአንድሪ ከተሞች የኮፕቲክ ክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች ላይ በደረሰው የሽብር አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ገለፁ፡፡
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለግብጹ አቻቸው H.E Sameh Shoukry በላኩት የሀዘን መግለጫ የጸሎት ስነስርዓት በሚያካሂዱ ንጹሃን ዜጎች ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት የደረሰውን የሞትና የመቁሰል አደጋ በማውገዝ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለግብጽ አቻቸው H.E. Mr. Sameh Shoukry የሀዘን መግለጫ ልከዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በሀዘን መግለጫቸው፣ የሽብር ጥቃቱ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ሊወገዝ የሚገባው እጅግ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መሆኑን ጠቁመው ሁኔታው መላው ዓለም የጸረ- ሽብር ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የሚያሳስብ ነው ብለዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለግብጹ አቻቸው በላኩት በዚሁ መልዕክት ለግብጽ ህዝብና መንግስት እንዲሁም ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ቤተሰቦች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው መጽናናትንም ተመኝተዋል፡፡

Spokesperson's Directorate General of the Ministry of Foreign Affairs of the Federal Democratic Republic of Ethiopia.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *